`

የዜጎች የስምምነት ሰነድ |
Citizens Charter

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ ለማደራጀት በወጣ አዋጅ ቁጥር 74/2014 መሰረት የሕብረተሰብ ተሳትፊና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን እንደገና የተቋቋመ ሲሆን ከተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መነሻ ለተገልጋዮቹ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በአዲስ መልክ በመለየት አደራጅቷል፡፡

ሀገራችን ብሎም ከተማችን እያካሄደች ያለውን የመሰረተ ልማት፣ የሰላምና ፀጥታ አጀንዳዎች፣የበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥን በስኬታማነት ከማጠናቀቅ አንፃር ፣ዘርፉ የሚጠይቀውን መሰረታዊ ችግሮች ለመቅረፍ ጥናቶችን በማጥናት ከዚህም ባሻገር በተለያዩ ደረጃዎች ባሉ ክፍለ ከተማ እና ወረዳዎች የሚከናወኑ በርካታ ተግባራትን ከመካከለኛ እስከ አመታዊ እቅድ ዝግጅት ስራ ድረስ የማሰባሰብ፣የመተንተንና የማጠቃለል፤የመርሀ ግብር አፈፃፀማቸውን የመከታተል፣የመደገፍ የመገምገምና ግብረ መልስ የመስጠት እና የመሳሰሉትን አበይት ተግባራት ለማከናወን የሚያስችልና ተገልጋዩም ከዚህ ተቋም ማግኘት ያለበትን አገልግሎቶች ግልፀኝነት መፍጠር የሚያስችለውን የዜጎች ቻርተርን እቅድ አዘጋቷል፡፡

ይህንን ኃላፊነትም በብቃት ለመወጣት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማዘጋጀትና በማሟላት በተገልጋዮች ጥያቄና ፍላጎት መሰረት የላቀ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም ፅ/ቤቱ የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋይ ፍላጎትን ማዕከል አድርጎ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር በማስቀመጥ የኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች ሊተገብሩትና ሊከተሉት የሚገባ ይህ የዜጎች ስምምነት ቻርተር ተዘጋጅቷል፡፡

የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ

በል/ክ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በአገልግሎት አሰጣጥ፣ በመሰረተ ልማት፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን ተሳትፎና ባህል በማጎልበት ችግሮችን ከምንጫቸው እንዲፈቱ በማድረግና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤እንዲሁም ይህ የስምምነት ሰነድ ኮሚሽኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዜጎች ህግና አሰራሩን ጠብቀው ያለምንም መሸራረፍ መብታቸውን በተሟላ መልኩ እንዲያገኙ ሲሆን ይህንንም ለአመራሩ፣ ለሰራተኛውም እና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ግልጽ ለማድረግ ከዚህም ባሻገር ደግሞ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በማይወጡ አካላት ላይም ተቋሙ የገባውን የህሊና ውል መሰረት አድርጎ የተጠያቂነት አሰራርን ለማጎልበት ያለመ ሲሆን ዝርዝር ዓላማውም፡-

  1. ማህበረሰቡ በሰላም፣ በልማት እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ የአመለካከት እና የአስተሳስብ ለውጥ እንዲያመጣና ተግባራዊ እንዲያደርጋቸው ማስቻል፤
  2. ብሎክን ማዕከል ያደረገ የህብረተሰብ ተሳትፎን በማጎልበት በነዋሪውና በከተማው አስተዳደር መካከል ያለውን ግንኙነት ማሳደግ፤፣
  3. ነዋሪዎችን በማሳተፍ በከተማው አስተዳደር የሚሰጠውን አገልግሎት በእኩልነት፣ በግልፅነት እና በፍትሀዊነት መርህ መሠረት እንዲያገኙ ማድረግ፤
  4. በከተማው አስተዳደር የልማት እቅዶችና በአፈፃፀማቸው ሂደት ነዋሪው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ እና የልማቱም ፍትሀዊ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል፤፤
  5. የነዋሪዎችን መስተጋብርና ትስስር በማጠናከር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በነዋሪው ንቁ ተሳትፎ እንዲቀረፉ ማድረግ፤
  6. በክፍለ ከተማ አስተዳደር እና በነዋሪው ንቁ ተሳትፎ በከተማው ሠላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ማስቻል፤
  7. የበጎ ፈቃድ ባህልን በማህበረሰቡ ዉስጥ ማጎልበት፤
  8. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሳተፉ በጎ ፈቃደኞች ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
  9. የከተማችንን ማህበረሰብ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ በማሳተፍ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፤

ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች (Starategic Themes)

  1. መዋቅራዊ የብሎክ አደረጃጀት እና የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ተሳታፊና ተጠቃሚ ማድረግ
  2. የሀብት አሰባሰብ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሀብትን በማፈላለግ ወደ ስራ በማስገባት የሀብት ብክነት እንዳይኖር ያስችላል፡፡፣
  3. የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር መፈጠር እና የበጎነት ባህሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣት፤
  4. ቀልጣፋና ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ በመስጠት የነዋሪውን መሰረታዊ ችግሮችን መፍታት፤
  5. ህገወጥነትን በመከላከል የብሎኩን ሰላምና ፀጥታ ማስጠበቅ የሚያስችል የካውንስል አደረጃጀትን በመዘርጋት ሊፈጠሩ የሚችሉትን ህገወጥና አዋኪ ድርጊቶችን ለመቀነስ እንዲሁም ነዋሪው በሰላም ወጥቶ በሰላም የሚመለስበት፤

የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት

    የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት በዝርዝር ለማወቅ ከፈለጉ ይህን Duties and Responsibility ይጫኑ

የተገልጋዮች መብት

  1. ምንም ልዩነት ሳይደረግበት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የመሆን፣
  2. ማንኛውም ተገልጋይ በአገልግሎቱ አሰጣጥና በአገልግሎት ሰጪው ቡድን/ሠራተኛ ላይ ያለውን አስተያየትና ቅሬታ የማቅረብ፣
  3. በጽ/ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዝርዝር የማወቅና የመጠቀም፤
  4. ተገቢ የሆነ ድጋፍና እገዛ የማግኘት፤
  5. ቀልጣፋ አገልግሎት የማግኘት፤

የተገልጋዮች ግዴታዎች

  1. ሕጎችንና የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
  2. ለሚፈልጉት አገልግሎት የተሟላና ትክክለኛ መረጃ የማቅረብ፣
  3. ተገልጋዬች አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ
    ተፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላት