• Vision

    የህብ/ተሳ/በጎ/ፈ/ማስ/ጽ/ቤት ራዕይ

    በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የልደታ ክፍለ ከተማ በ2022 ዓ.ም የለማ የህብረተሰብ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በጎ ፈቃድን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው፡:

  • Mission

    የህብ/ተሳ/በጎ/ፈ/ማስ/ጽ/ቤት ተልዕኮ

    በከተማው አስተዳደሩ ብሎክን ማዕከል ያደረገ የአግልግሎት አሰጣጥ፣ የመሠረተ ልማት፣ የፀጥታ ችግሮችን እና የበጎ ፈቃድ ተግባራት ፍላጎትን በመለየት የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጎልበት ችግሮችን ከምንጫቸው እንዲፈቱ በማድረግ የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፡፡

  • Assets

    የህብ/ተሳ/በጎ/ፈ/ማስ/ጽ/ቤት እሴቶች

    አሳታፊነት፡ ህብረተሰቡ በልማት፣በፀጥታና በአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ተግባራት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ፤
    ሰብአዊነት፡ በራስ ተነሳሽነነትና ፍላጎት ለሌላው ማህበረሰብ በጎ ተግባራትን መፈጸም፤
    ፍትሃዊነት፡ በብሎክ የሚገኙ ነዋሪዎች የሠላሙና የልማቱ በእኩልነትና በፍትሀዊነት ተቋዳሽ እንዲሆኑ ማስቻል እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ማህበራትን በማሰተባበር ፍትሀዊ አሰራርን ስርዓት መዘርጋት፤
    ተጠያቂነት፡ ነዋሪው ህብረተሰብ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚታዩትን ጉዳዮች የተጠያቂነት ስርዓት መዘርጋቱን ማረጋገጥ፤
    በዕውቀትና በእምነት መሥራት፡ መንግስት የሚሠጣቸው አገልግሎቶች ህብረተሰቡ እምነት እንዲኖራቸው ማድረግ፤
    ለለውጥ ዝግጁነት፡ አገልግሎት ሰጭውም ሆነ ተቀባዩ አካል ለለውጥ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ
    ችግር ፈቺነት፡ መንግስትና ነዋሪው ህብረተሰብ ለሚፈጠሩት ችግሮች መፍትሔ አምጪ እንዲሆኑ ማድረግ፤