በልደታ የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዋና ዋና ተግባራቶች
- 1. በሀብት ማሰባሰብና አቅም ማጎልበት ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- ጥናት ማካሄድ፣
- ለማህበረሰብ አቀፍ አደረጃጀቶች ንቅናቄ መፍጠር ፣
- ለብሎክ ነዋሪዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣
- አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መፈለግ፣ ፕሮጀክት ማበልጸግ፣ ሀብት ማሰባሰብ እና ማከማቸት፤፤
- በብሎክ አደረጃጀት ላይ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በመለየት ከሚመለከተው አካል ጋር እንዲፈታ ማመቻቸት፤
- 2. በሰላም እሴት ግንባታ ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- በብሎክ የደንብ ጥሰት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን በመለየት እርምጃ እንዲወሰድ ማስደረግ፤
- የብሎክ አደረጃጀትን በመጠቀም ሰላምና ጸጥታን የተመለከተ ወቅታዊ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ፤
- የብሎክ አደረጃጀትን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባራትን መከላከል፤
- በህብረተሰብ ተሳትፎ የአካባቢን ሰላምና ደህንነት መጠበቅ፤
- 3. በመሠረተ ልማት ቅንጅት ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የግንባታ ዲዛይን ማዘጋጀት፤
- የጨረታ ውለታ ማስተዳደር፤
- የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
- የሚገነቡ የመሰረተ ልማት ሥራዎች መረከብና ማስተዳደር፤
- የብሎክን እና የመሰረተ ልማት መረጃን መሰብሰብና ማደራጀት፤
- 4. በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቡድን የሚሰጡ አገልግሎቶች
- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማሰተባበር፤
- የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ግንዛቤ እና ማስረፅ፤
- የበጎ ፈቃድ ካውንስል ማሳተፍ፤
- ለበጎ ፈቃድ የተሰበሰበውን ሀብት ማሰራጨት፤
- በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ፤
- ደረጃ በህብረተሰብ ልማትና በበጎ ፈቃድ ተግባር ለተሳተፉ እውቅናና ማበረታቻ መስጠት፤