image
image
image
image
image

"የበጎ ፍቃድ ስራ ወሰን የለሽ የሰብዓነት ተግባር ነዉ" የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት

መስከረም 3, 2019
የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት «በጎ ፈቃደኝነት ለማህበረሰብ ለውጥ» በሚል መሪ ቃል በሸገር ሲቲ ለገጣፎ ለገዳዲ የወሰን የለሽ ፕሮግራም አካሄደ። የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ እንደገለጹት፤ ይህ የወሰን የለሽ የበጎ ፍቃድ ፕሮግራም በሸገር ሲቲ ለገጣፎ ለገዳዲ አካባቢዎች ላሉ ወገኖች የሚደረግ ድጋፍ ነዉ ብለዉ ይህ ተግባር ተርፎን ሳይሆን ካለን ላይ ለማካፈል ነዉ ብለዉ ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።ይህን ያደረግነዉ ከአጎራባች ከተሞች ጋር የአለንን አብሮነት ለመግለፅ ነው ብለዋል። ኃላፊው አክለውም፣ በጎ ፈቃደኝነት ለአገርና ለወገን ካለው ዘላቂ ጠቀሜታ አንጻር የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ነዋሪዎች በዚህ ታላቅ መርሃ-ግብር ላይ በንቃትና በቁርጠኝነት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። የሸገር ሲቲ ለገጣፎ ለገዳዲ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ አቶ አሰፋ መንግስቱ በበኩላቸዉ ለተደረገዉ ድጋፍ አመስግነዉ ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክታቸዉን አስተላልፈዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ