image
image
image
image
image

በልደታ ክፍለ ከተማ 'በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ' በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ።

ሀምሌ 1, 2019
"በጎነት ለአዲስ አበባ ከፍታ" በመርሐ ግብሩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የልደታ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ የተገኙ ሲሆን የበጎ ፈቃድ ተግባራት፤ ሰው ተኮር ስራዎች በመሆናቸው ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም ፓርቲና መንግስት በመኖሩ በፖሊሲዎች ውስጥ ተካተው እንዲተገበሩ ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። የዘንድሮው ክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት በተከታታይ አመታት ካደረግነው በላቀ መልኩ መነሳሳት የሚፈጥር ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ያለን በመሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪ ለዚህ በጎ አላማ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አቶ ዘመኑ ጥሪ አቅርበዋል። ኃላፊው አያይዘው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ የኢትዮጵያን አሸናፊነት በማረጋገጣችን እንኳን ደስ ያላችሁ ያሉ ሲሆን ምርጫው የተሳካ እንዲሆን የክፍለ ከተማው ነዋሪ ላሳየው ከፍተኛ ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል። የልደታ ክ/ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ በበኩላቸው በዚህ ክረምት 19 የበጎ ፈቃድ ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን በዛሬው እለትም ከ220 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ እና የደም ልገሳ መርሐ ግብር በይፋ የሚጀምር መሆኑ ገልፀዋል። የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረ ሲሆን በጎ ፈቃደኞች ደም በመለገስ ለወገን ደራሽነታቸው በተግባር አሳይተዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ