image
image
image
image
image

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የአብሮነት፣ የአንድነት፣ የመረዳዳት እና የፍቅር እሴትን የምናጎለብትባቸው ናቸው ሲል የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር ገለፀ

መስከረም 14, 2019
አስተዳደሩ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት አከባበር በማስመልከት ከበጎ ፈቃደኞች፤ ከቅጥር ጥበቃዎች እና ከብሎክ ካውንስል አባላት ጋር ውይይት አካሂዷል። የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከቅን አስተሳሰብ የሚመነጭ፣ ሰውን በበጎነት ለማገልገል ጊዜውን፣ ጉልበቱን፣ ገንዘቡን እና እዉቀቱን ያለ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ በቅንነት መስጠት መሆኑን ገልፀው፣ በጎ ፈቃድ ለሀገር ዕድገት፣ ለማህበረሰብ አንድነት ከቃል ባለፈ በተግባር ማገልገል በመሆኑ መስቀልና ኢሬቻን ለማክበር ወደ ከተማችን የሚመጡ ወንድምና እህቶቻችንን ተቀብለን በትጋት ማስተናገድ ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል። ለዓለም ያበረከትናቸው በዓላቱ ያለምንም ስጋት እንዲከበሩ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን መወጣት እንዳለበትም አቶ አሰፋ ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ በበኩላቸው ሀገራችን በርካታ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላትን ለአለም አበርክታለች ብለዋል። የመስቀል እና የኢሬቻ በዓላት አንድነትንና ወንድማማችነትን ከማጠናከር ባለፈ ለሀገር በጎ ገፅታ ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳላቸውም ገልፀዋል። የቅጥር ጥበቃ አባላት እና የብሎክ ካውንስል አመራሮችም ለፀጥታ ተቋማት ደጀን በመሆን በዓላቱ በሰላም እና በድምቀት ተከብረው እንዲያልፉ የበኩላቸውን አስተዋፅዖ መወጣት እንዳለባቸውም ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ