image
image
image
image
image

የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ገመገመ።

ሚያዚያ 14, 2017
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደተናገሩት ባለፉት 9 ወራት የበጎ አድራጎት ስራዎች በመሰራታቸው በርካታ አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው የቤት ዕድሳትን፣ነጻ የህክምና አገልግሎቶች፣የማጠናከሪያ ትምህርት፣የትራፊክ አገልግሎቶች፣የደም ልገሳና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎችን በማጠናከርና ክፍተቶችን በመሙላት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጉን መቀጠል ይገባል ብለዋል። አቶ እንግዳው አክለውም ዜጎች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ በመሆናቸው ከመንግስት የሚወጣ በጀትን ከመቀነሱም በላይ አቅመ ደካሞች ጉልበትና ገንዘብ ባላቸው ወጣቶችና ባለሃብቶች ተስፋ እንዲኖራቸው ማድረጉን ገልጸው የበጎ አድራጎት ስራዎችን ውጤታማነትን ለማስቀጠል ባለሃብቶች፣ ወጣቶች፣ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላት ከመንግስት ጋር በመተባበር ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ