image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ የ2017 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያ እና የ2018 ዓ.ም የበጋ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ተካሄደ

ህዳር 27, 2017
በፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ አራርሳ ድሪባ እንደተናገሩት በጎ ማድረግ የህሊና ዕረፍትን የሚሰጥ በገንዘብ ሊተመን የማይችል አንድነትና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር ተግባር ነው ብለው በዚህም በአስተዳደሩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማጠናከር መረዳዳትን፣ መደጋገፍንና መጠያየቅን ባህሉ ያደረገ ትውልድ እንዲፈጠር ለማስቻል ኃላፊነታችንን እየተወጣን ነው ሲሉ ገልፀዋል። አቶ አራርሳ አክለውም በ2017 ዓ.ም በክረምት ወቅት የተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ያረጋገጡ ናቸው ብለው ይህ ተግባር ግለቱን ጠብቆ በ2018 ዓ.ም በጋ ወቅትም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል። በጎ ፈቃደኞች በእውቀታቹህ፣ በጉልበታቹህና በገንዘባቹህ በመሳተፍ ለወገናቹህ ያላቹህን አለኝታነት አሳይታቹሃል ያሉት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው ለዚህ አስተዳደሩ ምስጋና ያቀርባል ሲሉ ገልፀዋል። በ2017 ክረምት የተከናወኑ የቤቶች ዕድሳት ፣ የማዕድ ማጋራት ፕሮግራሞች፤የክረምት ትምህርት፣የጤና እና የትራፊክ አገልግሎቶችን ለነዋሪዎች እንዲደርስ የሚደረገው ርብርብ ሊጠናከር የሚገባው መሆኑን የገለጹት አቶ አራርሳ በክረምት የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በጎ ምላሽ ለሰጡ መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት በአስተዳደሩ ስም አመስግነው ድጋፋቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል ብለዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደገለጹት በ2017 በጀት ዓመት በክረምት መርሃ ግብር የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላ፣ የአካባቢውን ጽዳት፣ የማዕድንና ማጋራት ፕሮግራምና የቤት ዕድሳት ፕሮግራሞች የተካሄዱ መሆናቸውን ገልጸው በክረምት የተመዘገበው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በበጋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባቸዋል ብለዋል። በፕሮግራሙ ማጠቃለያ በ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የምስጋናና እውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች