image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የጂ+4 የጋራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ተጀመረ

ህዳር 7, 2017
በክ/ከተማው አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርግ የጂ+4 የመኖሪያ ቤት ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የማስቀመጥ ፕሮግራም ተካሂዷል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በግንባታ ማስጀመሪያው እንደተናገሩት መሰረቱ ሰው የሆነው ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር ተግባራትን በማከናወን የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል ብለው ለዚህም ማሳያ በከተማዋ በተለያዩ ክ/ከተሞች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ህይወት በዘላቂነት ለመለወጥ እየሰራ መሰረታዊ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል በማለት ተናግረዋል። ብልፅግና ፓርቲ በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የዜጎችን ክብር የሚመጥኑ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል ያሉት አቶ አብዱልቃድር የሚገነባው የመኖሪያ ቤት የዜጎችን ተስፋ የሚያለመልም እና አኗኗራቸውን የሚያዘምን ነው በማለት ተናግረዋል። የጋራ መኖሪያ ቤቱ ሲጠናቀቅ የዜጎችን የቤት ችግር በማቃለል ረገድ ጠቀሜታ አለው ብለዋል አቶ አብዱልቃድር ። የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ፓርቲያችን ብልፅግና የዜጎችን መሰረታዊ ጥያቄዎች በመመለስ ረገድ ቁርጠኛ መሆኑን ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን ፓርቲው መልካም አስተዳደርን በማስፈን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ ከምንጊዜውም በላይ ይሰራል ሲሉ ገልፀዋል። ፓርቲያችን ብልፅግና የገባውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር እና ያቀደውን በመፈፀም ረገደድ ተወዳዳሪ የለውም ብለው ፓርቲው ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድም አሻራውን እያስቀመጠ ወደ ብልፅግና ጎዳና መትመሙን ይቀጥላል ሲሉ ገልፀዋል። በመጨረሻም የሀገራችን እድገት የሁላችንም ስራ ውጤት በመሆኑ ለሀገር እድገትና ብልፅግና እጅ ለእጅ ተያይዘን እንስራ ያሉት ወ/ሮ ልዕልቲ ለዜጎች ተጠቃሚነት 24/7 እየሰራን እንቀጥላለን በማለት ገልፀዋል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች