image
image
image
image
image

በልደታ ክ/ከተማ "የእያንዳንዱ ጥረት ለዉጥ ያመጣል" በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ተከበረ

ታህሳስ 5, 2017
በልደታ ክፍለ ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ''የእያንዳንዱ ጥረት ለዉጥ ያመጣል'' በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም አቀፍ የበጎ ፍቃደኞች ቀን ከብሎክ አደረጃጀትና ከልየታ ኮሚቴ ጋር የበጎ ፍቃድ አሰራርና የልየታ ግዛቤን በማወያየት ተከብሯል። በበጎ ፍቃድ ድጋፍ የሚለዩ የማህበረሰብ ክፍል በብሎክ አደረጃጀቶች አማካይነት በደረጃ በጥንቃቄ መለየት በዋናነት የሚሰራ ስራ ነዉ ተብሏል። የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እና የማህበራዊ ኃላፊነትን ለመደንገግ በወጣዉ ደንብ ቁጥር 161/2016 መሠረት እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል በተለይ ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶች፣ ማህበራት ወዘተ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣበት አሰራር መዘርጋቱን ተጠቁሟል። ከግንዛቤ ማስጨበጥና ዉይይት በኋላ ባለፈዉ ክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተሰሩ ስራዎችን የሚያሳይ ፎቶ አዉደ ርዕይ ተካሂዷል።

መልዕክትዎን ይላኩ

ሌሎች ዜናዎች