image
image
image
image
image

የልደታ ክ/ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት በክ/ከተማው 307 ብሎኮችን መልሶ በማደራጀት ይፋ አደረገ

ግንቦት 27, 2017
የልደታ ክ/ከተማ ኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ላለፉት አመታት አገልግሎት ላይ የነበረውን የብሎክ አደረጃጀት ክ/ከተማው በመልሶ ማልማት ውስጥ እንደመሆኑ መጠን ይሄን ታሳቢ በማድረግ መልሶ የማድራጀት ስራ በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት ይፋ የማድረግና የማስተዋወቅ መርሃ ግብር አካሂዷል :: በመልሶ ማደራጀቱም ከዚህ በፊት የነበሩ ብሎኮች የነበሩባቸውን ውስንነቶች መቅረፍ የሚያስችልና ለኅብረተሰቡ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑ በመድረኩ ተመላክቷል። የልደታ ክ/ከተማ ህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ እንግዳው ጓዴ እንደገለፁት የብሎክ አደረጃጀቱ ነዋሪው መሳተፍ በሚችልበት ጉዳይ በቀጥታ እንዲሳተፍ፣ የአካባቢውን ልማት በራሱና በመንግስት ትብብር እንዲያለማ እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ እና የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ እና የኅብረተሰቡን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች ለመፍታት የጎላ ሚና ያለው መሆኑን ገልፀዋል:: በተጨማሪም ክ/ከተማው በ307 ብሎክና በ2456 የብሎክ አመራሮች መልሶ መደራጀቱን በመድረኩ አብስረዋል:: በተጨማሪም ለተሳታፊዎች "የበጎ ፈቃድና አገልግሎትና ማህበራዊ ሀላፊነት ደንብ 161/2016 እንዲሁም በበጎ ፈቃድ ፅንሰ ሀሳብ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል:: ተሳታፊ በጎ ፈቃደኛና የብሎክ አመራሮች እንደገለፁት ከሆነ ስልጠናው ለክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች በተነቃቃ መንገድ ወደ ስራ እንድንገባ ያግዘናል ብለዋል::

መልዕክትዎን ይላኩ